Sign in

Ethiopique - ኢትዮጲክ

@ethiopique202.bsky.social
218 followers 22 following 184 posts

Local news and resources for Amharic speaking immigrant communities in DC-MD-VA. Web: www.ethiopique.com

PostsRepliesMedia
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 09/03/2026
Thank you to everyone who joined us as we marked four years of Ethiopique. We appreciate the support of Listening Post Collective and Documented, and thank Selam of Sheger Spring Cafe, our community members, and our team members Tsigereda and Abebayehu for making the listening session possible.
010
Reposted by Ethiopique - ኢትዮጲክ
Tiny News Collective @tinynewscollective.bsky.social · 04/03/2026
🎂 Happy Birthday to @ethiopique202.bsky.social Founded by Henok Mengistu four years ago, Ethiopique serves Amharic-speaking communities across DC, MD and VA. From hundreds of stories to community events, they are constantly uplifting Ethiopian & Eritrean voices. 🔗 ethiopique.com
ethiopique.com
Ethiopique-ኢትዮጲክ
A bridge to community.
131
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 15/02/2026
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት ነዋሪዎች ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ሳይሰጉ የመንግስት አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችለውን የትረስት አክት (Trust Act) በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። ይህ አዲስ ህግ የካውንቲው ሰራተኞች ያለ ህጋዊ ምክንያት የነዋሪዎችን የኢሚግሬሽን ሁኔታ እንዳይጠ.... ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ። ethiopique.com?p=7988 #ethiopique #AmharicNews #MontgomeryCounty #TrustAct #ImmigrantRights
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 17/10/2025
ባሳለፍነው ሰሞን ኦክቶበ 8 ከጧቱ 10፡24 ላይ አንዲት የ27 አመት ወጣት በኤ አይ በተፈጠረ ምስል በመጠቀም ለባለቤቷ አንድ ሰው ገፍትሯት ቤታቸው እንደገባ በቴክስት ትነግረዋለች። ይህንን ተከትሎም ባልየው ለፖሊስ በ911 ደውሎ ቤታቸው እየተዘረፈ እንደሆነ ይነግራቸዋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=7070
ethiopique.com
ከሰሞኑ የቲክቶክ ትሬንድ በነበረው ቪዲዮ ባሏን ፕራንክ ልታደርግ የሞከረች  አንዲት የሞንጎምሪ ካውንቲ ሴት ታሰረች
ባሳለፍነው ሰሞን ኦክቶበ 8 ከጧቱ 10፡24 ላይ አንዲት የ27 አመት ወጣት በኤ አይ በተፈጠረ ምስል በመጠቀም ለባለቤቷ አንድ ሰው ገፍትሯት ቤታቸው እንደገባ በቴክስት ትነግረዋለች። ይህንን ተከትሎም ባልየው ለፖሊስ በ911 ደውሎ ቤታቸው እየተዘረፈ እንደሆነ ይነግራቸዋል።  ፖሊሶችም ጉዳዩን ሊያጣሩ እንዲሁም ከተ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 17/10/2025
ስምዖን ጌታቸው የተባለ የ30 ዓመት ወጣት እሁድ ኦክቶበር 12 ምሽት በሳውዝ ኢስት ዋሽንግተን ዲሲ በጥይት ተመቶ መገደሉ ቤተሰቦቹንና ማህበረሰቡን በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ የከተተ ሲሆን፤ ወዳጅ ዘመዶቹ ገዳዮቹ ወደፍትህ እንዲቀርቡና ፍርድ እንዲያገኙ እየጠየቁ ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7064
ethiopique.com
የ30 ዓመቱ ስምዖን ጌታቸው በሳውዝ ኢስት ዲሲ በተተኮሰበት ጥይት ለህልፈት ተዳረገ። ወዳጅ ዘመዶቹ አግዙን ይላሉ
ስምዖን ጌታቸው የተባለ የ30 ዓመት ወጣት እሁድ ኦክቶበር 12 ምሽት በሳውዝ ኢስት  ዋሽንግተን ዲሲ በጥይት ተመቶ መገደሉ ቤተሰቦቹንና ማህበረሰቡን በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ የከተተ ሲሆን፤ ወዳጅ ዘመዶቹ ገዳዮቹ ወደፍትህ እንዲቀርቡና ፍርድ እንዲያገኙ እየጠየቁ ነው። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 16/10/2025
የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS)፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው (ፎርም I-589) ሞልተው መልስ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ግለሰቦች አመታዊ የጥገኝነት ክፍያ (Asylum Fee) እንዲከፍሉ የሚያዝ ደብዳቤዎችን መላክ ጀምሯል። ዝርዝሩ ethiopique.com?p=7059
ethiopique.com
ዩኤስሲአይኤስ አመታዊ የጥገኝነት አመልካቾች ክፍያ እንዲከፍሉ ለአመልካቾች ደብዳቤዎችን መላክ ጀመረ
የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS)፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው (ፎርም I-589) ሞልተው መልስ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ግለሰቦች አመታዊ የጥገኝነት ክፍያ (Asylum Fee) እንዲከፍሉ የሚያዝ ደብዳቤዎችን መላክ ጀምሯል። ጁላይ 4, 2025 በጸደቀው ቢግ ቢውቲፉል ቢል ላይ ከያዝነው የበጀት አ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 15/10/2025
... ያኔ ወላጆችን ሳይ እንዲሁም አንዳንዴ ደግሞ ትልልቅ ሰዎችም ሲገቡ እስር ቤት ውስጥ የባህል አለመግባባት ይኖራል እና በጣም ያሳዝኑኝ ነበረ ። አንዴ በጣም የማይረሳኝ፦ አንድ ሰውዬ የሽንት ችግር ነበራቸው። እና በጣም ሽንት ሲያስቸግራቸው፤ ሞል ውስጥ ከመኪናቸው ጎን ወደ ዳር ሆነው ሸኑ። ሲሸኑ ያዩአቸው ነጮች ደወሉባቸው እና ታስረው መጡ። ... ዝርዝሩ ..👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=7051
ethiopique.com
ዶ/ር ሊሻን ካሳ የምስጋና ምሽት ተዘጋጀላቸው
የኢትዮጲክ ባልደረቦች ከሰሞኑ ከቀድሞዋ የሞንጎምሪ ኮሚውኒቲ ኮሌጅ የኢስት ካውንቲ ዳይሬክተር ከነበረችው ዶክተር ሀምራዊት ግብዣ ይደርሳቸዋል፡፡ ይህ ግብዣ ደግሞ ለበርካቶች አገልግሎትን የሰጠችውን ዶክተር ሊሻን ካሳን ለማመስገንና ዕውቅና ለመስጠት የተደረገ ፕሮግራም ላይ እንድንገኝ የሚጋብዝ መልዕክት ነበር፡፡ ታ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 14/10/2025
እንደ ባልቲሞር ፖሊስ መምሪያ ተጠርጣሪዎቹን የ32 ዓመቱ ኤፍሬም መለክቴ እና የ67 ዓመቷ ፋሲካ ጻዲቅ መሆናቸውን ይፋ ቢያደርግም፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በርካታ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች አሁንም ድረስ አሉ። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=7031
ethiopique.com
የአቶ መኮንን ገዳይ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በኒውዮርክ መያዛቸው ታወቀ፤ በተጠርጣሪዎቹና በሟች መካከል ስለነበረው ግንኙነትና የግድያው መንስኤ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል
ባሳለፍነው ሰሞን ባጋራናችሁ ዜና የባልቲሞር ነዋሪ የነበሩት የ71 አመቱ አዛውንት አቶ መኮንን ሀብተስላሴ ሴፕቴምበር 25 ቀን በምስራቅ ባልቲሞር በ1200 ብሎክ የኖርዝ ፓተርሰን ፓርክ አቬኑ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተገለው እንደተገኙና ፖሊስም ገዳዮችን ለመያዝ ምርመራ እያደረገ እንደነበር ይታወቃል። ፖሊስ ታ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 14/10/2025
በሎርተን ከተማ በተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ ምክንያት በአንድ ማይል ራዲየስ ያሉ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ አስጠነቀቀ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7043
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 12/10/2025
በአብቹ ለማ የፌዴራል መንግስት ከተዘጋ ወደ ሁለተኛ ሳምንት ተሸጋግሯል። ቀኑ በተራዘመ ቁጥር በሠራተኞች፣ በቤተሰቦቻቸውና በአገልግሎት ሰጪ ቢዝነሶች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። ከዚህ አንፃር በቨርጂኒያ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል መለስተኛ ቅኝት አድርገናል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7026
ethiopique.com
የፌዴራል መንግስት መዘጋት በቨርጂኒያ የሚኖሩ የፌዴራል ሠራተኞችና ቢዝነሶች ላይ ያስከተለው ተፅዕኖ
በአብቹ ለማ  የፌዴራል መንግስት ከተዘጋ ወደ ሁለተኛ ሳምንት ተሸጋግሯል። ቀኑ በተራዘመ ቁጥር በሠራተኞች፣ በቤተሰቦቻቸውና በአገልግሎት ሰጪ ቢዝነሶች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። ከዚህ አንፃር በቨርጂኒያ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል መለስተኛ ቅኝት አድርገናል።   በቨርጂኒያ የሚገኙ የፌዴራል…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 11/10/2025
የትራምፕ አስተዳደር የመንግስት መዘጋቱ በዚሁ ከቀጠለምና ወደ ኖቨምበር ከተሻገረ የፉድ ስታምፕ ተጠቃሚዎችን የድጎማ ገንዘብ ለመሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ስለማይኖር ስቴቶች ለፉድ ስታምፕ ደንበኞች ገንዘብ እንዳይልኩ አስጠነቀቀ። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7020
ethiopique.com
የመንግስት በጀት በኮንግረስ ካልተፈቀደ ስቴቶች ፉድ ስታምፕ እንዳይሰጡ ታዘዘ
የትራምፕ አስተዳደር የመንግስት መዘጋቱ በዚሁ ከቀጠለምና ወደ ኖቨምበር ከተሻገረ የፉድ ስታምፕ ተጠቃሚዎችን የድጎማ ገንዘብ ለመሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ስለማይኖር ስቴቶች ከኖቨምበር ጀምሮ ለፉድ ስታምፕ ደንበኞች ገንዘብ እንዳይልኩ አስጠነቀቀ። ይህ ማስጠንቀቂያ ከኮቪድ ወረርሺኝ በኋላ በተለይም የምግብ ዋስትና እ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 11/10/2025
የፌደራል መንግስት አስረኛ ቀኑን ይዞ በቀጠለው የመንግስት መዘጋት ወቅት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ ሰራተኞችን በቋሚነት ከስራ የማሰናበት ደብዳቤዎችን (ኢሜይሎችን) መላክ ጀምሯል። ዛሬ ዓርብ ኦክቶበር 10 የፌደራል መንግስቱ የበጀትና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ረሰል ቮውት በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ “የአር.አይ.ኤፍ (RIF) ርምጃ ተጀምሯል” ሲሉ አስታውቀዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7017
ethiopique.com
አስረኛ ቀኑን የያዘውን የመንግስት መዘጋት ተከትሎ የፌደራል መንግስት ለበርካታ ሰራተኞች ከስራ ማሰናበቻ ደብዳቤዎችን ላከ
የፌደራል መንግስት አስረኛ ቀኑን ይዞ በቀጠለው የመንግስት መዘጋት ወቅት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ ሰራተኞችን በቋሚነት ከስራ የማሰናበት ደብዳቤዎችን (ኢሜይሎችን) መላክ ጀምሯል። ዛሬ ዓርብ ኦክቶበር 10 የፌደራል መንግስቱ የበጀትና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ረሰል ቮውት በኤክ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 10/10/2025
የዲስትሪክቱ የቅጥር ተሽከርካሪዎች መምሪያ (Department of For-Hire Vehicles ) በዩኒየን ስቴሽን ዙሪያ ስላሉ ህጎች ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ኦፕሬተሮች ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ኤጀንሲው እንደገለጸው፣ ደንቦቹ በከተማዋ ከሚገኙ በጣም በተጨናነቁ የትራንስፖርት ማዕከላት አንዱ በሆነው በዚህ ስፍራ የተሳፋሪዎችን፣ የአሽከርካሪዎችን እና የጎብኚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የወጡ ናቸው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7013
ethiopique.com
ዲኤፍኤችቪ (DFHV) በዩኒየን ስቴሽን በራፍ ስለሚኖሩ ጥብቅ ደንቦች ለታክሲ አሽከርካሪዎች ማሳሰቢያ ሰጠ
የዲስትሪክቱ የቅጥር ተሽከርካሪዎች መምሪያ (Department of For-Hire Vehicles ) በዩኒየን ስቴሽን ዙሪያ ስላሉ ህጎች ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ኦፕሬተሮች ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ኤጀንሲው እንደገለጸው፣ ደንቦቹ በከተማዋ ከሚገኙ በጣም በተጨናነቁ የትራንስፖርት ማዕከላት አንዱ በሆነው በዚህ ስፍራ የተሳፋ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 10/10/2025
አመታዊው የዩ ኤስ አርሚ የ10 ማይል ሩጫ ውድድርን በማስመልከት ዕሁድ ኦክቶበር 12 በዲሲ የሚገኙ በርካታ መንገዶች ላይ መኪና ማቆምም ሆነ ማሽከርከር እንደማይፈቀድ የዲሲ ፖሊስ አስታውቋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7010
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 09/10/2025
የዩኤስሲአይኤስ (USCIS) ዳይሬክተር ጆሴፍ ኤድሎው የኢሚግሬሽን ማጭበርበርን እና የጥገኝነት (Asylum) ክምችትን ለመቀነስ እየሰሩ እንደሆነ አስታወቁ ዝርሩ 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6981
ethiopique.com
የዩኤስሲአይኤስ (USCIS) ዳይሬክተር የኢሚግሬሽን ማጭበርበርን እና የጥገኝነት (Asylum) ክምችትን ለመቀነስ እየሰሩ እንደሆነ አስታወቁ
የአሜሪካ ዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች (U.S. Citizenship and Immigration Services – USCIS) ዳይሬክተር የሆኑት ጆሴፍ ኤድሎው በቅርቡ ሴንተር ፎር ኢሚግሬሽን ስተዲስተዲስ (Center for Immigration Studies) ባዘጋጀው ውይይት ላይ እየተተገበሩ ያሉ ዋና…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 08/10/2025
በአብቹ ለማ የዋሽንግተን ፖስት የኖቨምበር 2021 ዘገባ እና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የፌቡራሪ 2025 የጥናት ውጤት በኖቨምበር 2/2021 በተካሄደው የቨርጂኒያ ምርጫ ዲሞክራቶችን ይደግፉ የነበሩ ኢትዮ-አሜሪካውያን ሳይቀሩ የሪፐብሊካኖችን ተወካይ ግሌን ያንኪንን እንደመረጡ ያመላክታል። የዚህ ገፊ ምክያንት ደግሞ በወቅቱ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተከተለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከኢትዮጵያውያንና… ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6975
ethiopique.com
በቨርጂኒያ 2025 የገቨርነሮች ምርጫ ኢትዮ-አሜሪካዊያን ማንን ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል? የምርጫ መሥፈርቶቻቸውስ ምንድናቸው?
በአብቹ ለማ  የዋሽንግተን ፖስት የኖቨምበር 2021 ዘገባ እና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የፌቡራሪ 2025 የጥናት ውጤት በኖቨምበር 2/2021 በተካሄደው የቨርጂኒያ ምርጫ ዲሞክራቶችን ይደግፉ የነበሩ ኢትዮ-አሜሪካውያን ሳይቀሩ የሪፐብሊካኖችን ተወካይ ግሌን ያንኪንን እንደመረጡ ያመላክታል። የዚህ ገፊ ምክያንት…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 07/10/2025
ቆይታ ከኢትዮጲክጋ – መክሊት ሀደሮ ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6983
ethiopique.com
ቆይታ ከኢትዮጲክጋ – መክሊት ሀደሮ
“አልበሜ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ባህር በትንሹ የተጨለፈ መሆኑን ለማሳየት ጥሬያለሁ” መክሊት ሀደሮ ኢትዮጲክ: መክሊት ሀደሮ ሙሉ አልበምሽ ኤ ፒስ ኦፍ ኢንፊኒቲ “A Piece of Infinity” በመውጣቱ እንኳን ደስ አለሽ እንዲሁም እንኳን ወደ ኢትዮጲክ በሰላም  መጣሽ።መክሊት ሀደሮ : ስ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 07/10/2025
ማስታወቂያ ... አፍሪክጎ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያለ ለወዳጅ ዘመድ መላክ የምትፈልጉት እቃ ካለ እኛ እንላክልዎ ይሎታል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (571)-315-7834 ወይንም በ (240)-641-8828 ይደውሉ::
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 07/10/2025
በአብቹ ለማ የፌደራል መንግስት ከኦክቶበር 1/2025 እኩለ-ሌሊት ጀምሮ በከፊል መዘጋጀቱ ከታወቀ በኋላ የዲሲ ከንቲባ ብሎም የሜሪላንድና የቨርጂኒያ ገቨርነሮች የፌደራል ሠራተኞችን ለመደገፍ የተናጠልና የጋራ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ከጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ጋር በዚህ ፅሑፍ ውስጥ ተካተው ቀርበዋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6977
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 05/10/2025
Yesterday we wrapped up our final Fishing with Ethiopique of 2025. East Potomac Park was closed due to the shutdown, but we found a new spot and still had a great turnout. Thank you to everyone who joined us this season; until we meet again when the weather gets warm. #FishingWithEthiopique
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 03/10/2025
ማስታወቂያ .. ማንኛውንም እቃ ወደ ኢትዮጵያ እንልካለን + እናመጣለን ! አድራሻ 3819C S George Mason Dr, Falls Church, VA 22041 ስልክ 571-579-1286 ወይም 571-579-0939 ዋሳ ኤክስፕረስ - የልብ አድርስ
010
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 03/10/2025
በዚህ ፕሮግራም ላይ ታዲያ የተለመዱትን ሽልማቶች ለአሸናፊ ልጆች ያዘጋጀን ሲሆን በዚህ ወር ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው አሸናፊዎችን የ50$ ጊፍት ካርድ ሳይሆን የ100$ ጊፍት ካርድ በ3 ዘርፍ ለሚያሸንፉ ታዳጊዎች (እድሜያቸው ከ15 ያነሱ) የምንሸልም ይሆናል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6966
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 30/09/2025
የአሌክሳንድርያ ፖሊስ የ62 ዓመት አዛውንት የሆኑትን አቶ ፍቅሬን አፋልጉኝ ብሏል። ለመረጃው የዘወትር አንባቢያችንን አንተነህን dደመላሽን እናመሰግናለን። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6904
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 30/09/2025
የዋይት ኃውስ በጀት ጽህፈት ቤት ኮንግረስ እ.ኤአ ከዛሬ ከመስከረም 30/2025 ቀነ-ገደብ በፊት በጀት ማፅደቅ ካልቻለ ተጨማሪ የፌዴራል ሰራተኞች ከሥራቸው ሊባረሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6903
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 29/09/2025
ማስታወቂያ ... አፍሪክጎ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያለ ለወዳጅ ዘመድ መላክ የምትፈልጉት እቃ ካለ እኛ እንላክልዎ ይሎታል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (571)-315-7834 ወይንም በ (240)-641-8828 ይደውሉ::
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 27/09/2025
ማስታወቂያ . . . ታዋቂዋ አርቲስት መክሊት ሀደሮ በመጪው ወር ኦክቶበር 18 2025 ላይ ከምሽቱ 8pm ጀምሮ ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው የሞንጎምሪ ኮሚውኒቲ ኮሌጅ ለ6 አመታት የለፋችበትን "ኤ ፒስ ኦፍ ኢንፊኒቲ" የተሰኘውን አልበም ታስመርቃለች። በዚህ የአልበም ምርቃት ላይ እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ይህን ሊንክ ተጭነው የመግቢያ ትኬቱን ማግነት ይችላሉ። bit.ly/meklith
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 27/09/2025
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከኦክቶበር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ አዳዲስ ታሪፎችን ከውጭ ኢምፖርት በሚደረጉ መድኃኒቶች፣ በከባድ መኪናዎች እና በቤት ፈርኒቸሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6889
ethiopique.com
ፕሬዘደንት ትራምፕ ከኦክቶበር 1 ጀምሮ ወደ ከውጭ ኢምፖርት በሚደረጉ እቃዎች ላይ አዲስ ታሪፍ ጣሉ
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከኦክቶበር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ አዳዲስ ታሪፎችን ከውጭ ኢምፖርት በሚደረጉ መድኃኒቶች፣ በከባድ መኪናዎች እና በቤት ፈርኒቸሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል።  ይህ የቀረጥ ፕሮግራም በዋናነት የአገር ውስጥ ምርቶችን ለማሳደግና እንደሀገር በሌሎች አ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 27/09/2025
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ ጆ ማሞ እና ሰይፉ ፋንታሁን በዋሽንግተን ዲሲ ሊሸለሙ ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6882
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 24/09/2025
በአብቹ ለማ ለኢትዮጲክ የተዘጋጀ የሞንጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ሰርጀንት ፓትሪክ ኬፕ I-270 ሃይ ዌይ ላይ በሰዓት 110 ማይል እያሽከረከረ የነበረውን ራፋኤል ማዮርጋ የተባለ የ21 ዓመት .. ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6822
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 23/09/2025
የኢትዮጲክ ባልደረቦች ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ኦቲዝም ማህበረሰብ መስራችና ፕሬዘደንት ከወይዘሮ አዜብ አታሮ ጋር ቆይታ አድርገናል። ይከታተሉት 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6818
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 21/09/2025
ልጆችዎት ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ይማራሉ? እንግዲያውስ ይህን ያንብቡ። ኮሌጅ ፓርክ በሚገኘው የሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎችና ሰራተኞች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሰውነት (የልብስ) ቅማል መገኘቱን ተከትሎ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር አስታውቋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6814
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 21/09/2025
ይህ መጠይቅ የኢትዮ-አሜሪካውያን ማህበረሰብ መሪዎቻቸውን ለመምረጥ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመሰብሰብ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በምላሾች በመንተራስ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ለመረዳትና የምናወጣቸውን መረጃዎች በአንባቢዎች ፍላጎት ለማዘጋጀት ይረዳናል። ሁሉም መልሶች ምስጢራዊነታቸው የተጠበቀ ሲሆን ምንም አይነት ማንነትዎችን የሚገልጽ መረጃ እንዳያስቀምጡ እንመክራለን። ሊንኩን ተከትለው በመሄድ መጠይቁን ይሙሉል forms.office.com/r/m4PKAxYyYj
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 19/09/2025
ከቀጣዩ ወር አንስቶ የአሜሪካ ዜግነት ለመሆን የሚፈልጉ ግሪን ካርድ ያላቸው ነዋሪዎች አዲስ እና ከቀደመው ብዛት ያለው ጥያቄዎች የሚቀርቡበት የዜግነት ፈተና እንደሚወስዱ uscis በዚህ ሳምንት ረቡዕ እ.ኤ.አ መስከረም 19/2015 ይፋ አድርጓል። የኢትዮጲክ ባልደረቦች ይህን ከግንዛቤ በማስገባት አንባቢዎች በድረ-ገጻችን ላይ የዜግነት ጥያቄዎችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲለማመዱ የሚያገለግል ጥያቄና መልስ ማቅረብ ጀምረዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6804
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 19/09/2025
የአሌክሳንድሪያ ከተማ በ811 ኖርዝ ኮለምበስ ስትሪት ላይ በሚገኘውና ዘ ዋይትሊ (The Whitley) በሚባለው አዲስ ባለ 78 ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ የሚገኙ 8 አፓርታማዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች በሎተሪ ለመሸጥ ማስታወቂያ አውጥቷል። በዚህ መሰረትም አመታዊ ገቢያቸው እስከ 114,800 ዶላር ያሉ በከተማዋ የሚኖሩ ወይንም የሚሰሩ ሰዎች ማመልከት ይችላሉ ብሏል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6795
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 18/09/2025
እኛም በዘንድሮው ዝግጅት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የምትሳተፈውን ፍሬህይወት ቢረጋን አነጋግረን ነበር፣ የፌስቲቫሉን ገጽታ እና ለዝግጅቱ ያላትን ዝግጅት በተመለከተ ከኢትዮጲክጋ ያረገችውን ቆይታ እነሆ ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6785
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 17/09/2025
የዩ.ኤስ. የተወካዮች ምክር ቤት በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በታዳጊዎች የሚፈጸሙ ወንጀለኞችን አያያዝና ፍርድ በእጅጉ የሚቀይሩ በሪፐብሊካን ተወካዮች የቀረቡ ሁለት አወዛጋቢ ረቂቅ ህጎችን አጽድቋል። እነዚህ እርምጃዎች  ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወንጀልን የመከላከል አጀንዳ ጋር የሚስማማና ሰፋ ያለ የሪፐብሊካን መሪዎች ግፊት ያለበት ረቂቅ ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6754
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 16/09/2025
እጬዎችን በደረጃ በመለየት የመምረጫ ዘዴ (Ranked Choice Voting) በአንድ ጊዜ ከአንድ ዕጩ በላይ ለመምረጥ የሚያስችል ዘዴ ነው። ይህ የምርጫ ዘዴ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ አውስትራሊያ፣ ኒው ዚላንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም በመሣሠሉት ሃገራት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል። በአሜሪካ ቨርጂኒያን ጨምሮ በ28 ስቴቶች በሥራ ላይ ውሏል። በአብቹ ለማ የተዘጋጀ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6736
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 16/09/2025
ዛሬ ከሞንጎምሪ ካውንቲ ካውንስል የወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ለአምስተኛ ጊዜ የሚያካሂደው ዓመታዊ የአፍሪካ ማንነትና ቅርስ ወር ክብረ በዓል ማክሰኞ ሴፕቴምበር 16፣.. ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6741
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 15/09/2025
!!እናመሰግናለን!! We are grateful to receive this citation from the Montgomery County Council ; something we didn’t even know existed. Grateful to the Ethio-American Chamber of Commerce for advocating for us and other businesses. It’s a reminder that strong networks open doors. Thank you 🙏🏾🙏🏾
010
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 12/09/2025
We now have included sample US Citizenship question for our readers to test their skills. Click the link to check out the prototype. 👉🏾 ethiopique.com?p=6693
010
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 11/09/2025
ከአምስቱ የቨርጂኒያ የሕዝብ ት/ቤቶች መካከል በፌርፋክስና በአርሊንግተን ካውንቲዎች የሚገኙት የፌዴራል ትምህርት ዲፖርትመንትን ለትራንስጀንደር ተማሪዎች መብት ተቆርቁራችኋል በሚል ፈንድ ማገዱ አግባብነት የለውም በማለት ያቀረቡት ክስ ውድቅ ተደርጓል። በአብቹ ለማ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6693
ethiopique.com
በቨርጂኒያ የሕዝብ ት/ቤቶችና በፌዴራል የትምህርት ዲፓርትመንት መካከል የተፈጠረው መካረር አሁንም እልባት አላገኘም!
በአብቹ ለማ ከአምስቱ የቨርጂኒያ የሕዝብ ት/ቤቶች መካከል በፌርፋክስና በአርሊንግተን ካውንቲዎች የሚገኙት የፌዴራል ትምህርት ዲፖርትመንትን ለትራንስጀንደር ተማሪዎች መብት ተቆርቁራችኋል በሚል ፈንድ ማገዱ አግባብነት የለውም በማለት ያቀረቡት ክስ ውድቅ ተደርጓል። በሴፕቴምበር 5/2025 በተካሄደው የፍርድ አሰጣጥ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 11/09/2025
መልካም የኢትዮጵያ አዲስ አመት እንመኝላችኋለን! We wish you a Happy Ethiopian New Year!!
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 10/09/2025
መልዕክቱም “በፎቶግራፍ የተደገፈ የቅጣት ማስረጃ መሠረት እርስዎ በዲኤምቪ አካባቢ ሲያሽከረክሩ ከሌሎች ይልቅ ለመኪና ግጭት ተጋላጭ ነዎት። ለራስዎና ለሌሎች ደህንነት ሲሉ የፍጥነት ወሰንንና የቀይ መብራት ደንቦችን በማክበር ያሽከርክሩ።” የሚል መልዕክት ሰዷል። በአብቹ ለማ ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6694
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 09/09/2025
የዛሬ የኢትዮጲክ እንግዳችን ወይዘሮ ሳራ ናቸው። ወይዘሮ ሳራ በሶሻል ሚድያና በበርካታ መጽሀፎቻቸው ስለ ልጅ አስተዳደግና ስለ ወላጅነት ጠቃሚ መረጃዎችን ለማህበረሰባችን ያደርሳሉ። ከወይዘሮ ሳራጋ ያደረግነውን ቆይታ እነሆ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6715
ethiopique.com
ቆይታ ከኢትዮጲክጋ – ሳራ ዘመኑ ሰናይ
ኢትዮጲክ- በቅድሚያ እንኳን ለኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም አደረሰዎ። እንግዳችን ስለሆኑ እናመሰግናለን። እስቲ ለአንባቢዎቻችን ማንነቶትን እና ሥራዎን ያስተዋውቁልን።ወ/ሮ ሳራ – እንኳን አብሮ አደረሰን። እኔም ስለጋበዛችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ። ሙሉ ስሜ ሳራ ዘመኑ ሰናይ ይባላል። የምኖረው በቨርጂኒያ ግዛት…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 08/09/2025
ዛሬ ሴፕቴምበር 8 በዋለው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ በሎስ አንጀለስ በሰፊው ይከናወኑ የነበሩ የአይስ ወረራዎችንና ስደተኞችን በጅምላ የማፈስ ስራ እንዲቀጥል ፈቅዷል፡፡ ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6684
ethiopique.com
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት  በአይስ (ICE) ላይ ተጥሎ የነበረው እቀባ እንዲነሳ ወሰወሰነ
ዛሬ ሴፕቴምበር 8 በዋለው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ በሎስ አንጀለስ በሰፊው ይከናወኑ የነበሩ የአይስ ወረራዎችንና ስደተኞችን በጅምላ የማፈስ ስራ እንዲቀጥል ፈቅዷል፡፡ ከዚህ ቀደም በስር ፍርድ ቤቶች አይስ ማንኛውንም ሰው የሌላ አገር ዜጋ ስለመሰለ ወይንም ሌላ ቋንቋ ስለተናገሩ ብቻ ማስቆምና…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 06/09/2025
የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች (USCIS) ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው ደንብ መሰረት ከዚህ ቀደም ያልነበረውና የስደተኞችን ጉዳዮ ከመመርመር የዘለለ አዲስ የሕግ ማስከበር ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6676
ethiopique.com
የUSCIS (የዩናይትድ ስቴትስ ኢሚግሬሽን ቢሮ) ከመጪው ወር ጀምሮ የራሱ ፖሊሶችና ኤጀንቶች እንዲኖሩት መመሪያ ቀረበ
የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች (USCIS) ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው ደንብ መሰረት ከዚህ ቀደም ያልነበረውና የስደተኞችን ጉዳዮ ከመመርመር የዘለለ አዲስ የሕግ ማስከበር ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ተቋሙ የአሜሪካን የኢሚግሬሽን ህግ የሚጥሱ ሰዎችን የሚመረምሩ፣ የሚያስሩ እና ጉዳያቸውን ወደ ፍ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 06/09/2025
ዛሬ ሴፕቴምበር 6, 2025፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ማይክ ጆንሰን ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ አስደንጋጭ መረጃ ለቀዋል። ለወራተ በኤፕስቲን ጉዳይ ሲብጠለጠሉ የከረሙት ፕሬዘደንት ትራምፕ ኤፍ ቢ አይ በኤፕስቲን ላይ በነበረው የወንጀል ምርመራ ወቅት በቀጥታ የኤፍ ቢ አይ ሰላይ (ጆሮ ጠቢ) እንደነበሩ ጠቁመዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6671
ethiopique.com
ፕሬዘደንት ትራምፕ የኤፍ ቢ አይ ጆሮ ጠቢ ነበሩ ተባለ
ዛሬ ሴፕቴምበር 6, 2025፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ማይክ ጆንሰን ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ አስደንጋጭ መረጃ ለቀዋል። ለወራተ በኤፕስቲን ጉዳይ ሲብጠለጠሉ የከረሙት ፕሬዘደንት ትራምፕ ኤፍ ቢ አይ በኤፕስቲን ላይ በነበረው የወንጀል ምርመራ ወቅት በቀጥታ የኤፍ ቢ አይ ሰላይ (ጆሮ …
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 06/09/2025
በዋሽንግተን ዲሲ የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ዣኒን ፒሮ፣ የዲ.ሲ. ካውንስል የታዳጊ ወንጀለኞችን አያያዝ ላይ በጣም የላላ አሰራር እንደሚጠቀምና ይህም ወንጀለኞች የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓል ሲሉ ክስ ካቀረቡ በኋላ ውዝግብ አስነስተዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6668
ethiopique.com
የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ዣኒን ፒሮ የዲ.ሲ. ካውንስል አባላት ታዳጊ ወንጀለኞችን ባእግባቡ አይቀጡም ሲሉ ከሰሱ
በዋሽንግተን ዲሲ የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ዣኒን ፒሮ፣ የዲ.ሲ. ካውንስል የታዳጊ ወንጀለኞችን አያያዝ ላይ በጣም የላላ አሰራር እንደሚጠቀምና ይህም ወንጀለኞች የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓል ሲሉ ክስ ካቀረቡ በኋላ ውዝግብ አስነስተዋል። ይህ ክስ የዲሲ መንግስት በሕዝብ ደህንነት ላይ እየጨመረ ያለውን ስጋ…
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 05/09/2025
ማስታወቂያ ___ መጠይቁን ለመሙላት ይህን ይጫኑ 👉🏾 bit.ly/4genux9
000
Ethiopique - ኢትዮጲክ @ethiopique202.bsky.social · 05/09/2025
ሞንጎመሪ ካውንቲ እሁድ ሴፕቴምበር 14 2025 ቀን በዊተን ሪጅናል ፓርክ 11ኛውን ዓመታዊ የወዳጅነት ፒክኒክ ያካሂዳል። ይህ የወዳጅነት ፕሮግራም ከሁሉም ባህል፤ ዘርና የሃይማኖት አይነቶች የተውጣጡ ሰዎችን በአንድ በማገናኘት ከልዩነት ይልቅ አንድነትን ለማጠናከር የታሰበ ፕሮግራም ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6661
ethiopique.com
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ሴፕቴምበር 14 ላይ ዓመታዊ የወዳጅነት ፒክኒክ ያዘጋጃል።
ሞንጎመሪ ካውንቲ እሁድ ሴፕቴምበር 14 2025 ቀን በዊተን ሪጅናል ፓርክ 11ኛውን ዓመታዊ የወዳጅነት ፒክኒክ ያካሂዳል። ይህ የወዳጅነት ፕሮግራም ከሁሉም ባህል፤ ዘርና የሃይማኖት አይነቶች የተውጣጡ ሰዎችን በአንድ በማገናኘት ከልዩነት ይልቅ አንድነትን ለማጠናከር የታሰበ ፕሮግራም ነው። ዝግጅቱ ከእኩለ ቀን ጀም…
000